ከአባቱ ጃፈር ጣሀ ከእናቱ ሰዓዳ አሊ በ2004 ዓ.ም የተወለደውና ገና በአፍላ እድሜው የብስክሌት ስፖርት የጀመረው አሚር በኢትዮጵያ በተለያዩ ውድድሮች የተሳተፈ ተወዳዳሪ ሲሆን ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ወክሎ እስከ አውሮፓ ተሻግሮ በተለያዩ ስድስት ሀገራት ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ሀገሩን በመወከል ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ነው። በዚህም በዩሲ አይ UCI ለአንድ አመት ወድድር ያካሄደ ወጣት ነው።
Amir, born in 2004 to his father Jafer Taha and mother Saada Ali, is a competitive cyclist who began the sport at a young age. He has participated in various competitions across Ethiopia and, through his remarkable achievements, earned a place on the Ethiopian national team. Representing his country, he expanded his reach beyond Africa to compete in races across six nations, establishing himself as a successful and impactful athlete. His accomplishments also include competing in a one-year tournament organized by the Union Cycliste Internationale (UCI), further highlighting his dedication and talent as a young cyclist.
አሚር ያስመዘገባቸው ውጤቶች
1. የብልፅግና ቀን አስመልክቶ በተደረገ ውድ ድር ሁለተኛ
2. የብሄር ብሄረሰብ ቀንን አስመልክቶ በተደረገ ውድድር የመጀመሪያ ሳምንት አንደኛ፣ እንዲሁም በሁለተኛ ሳምንት ሁለተኛ እና ባጠቃላይ ውጤት አንደኛ በመሆን አጠናቋል ።
3. የድሬ ታህሳስ ከአራት የውድድር መድረክ ደረጃ ውስጥ በመግባት ያጠናቀቀ የመጀመሪያ ዙር ስድስተኛ በሁለተኛ ቀን ውድድር ሁለተኛ በሶስተኛ ቀን ውድድር ስድስተኛ እንዲሁም አራተኛ ቀን ውድድር ሶስተኛ በመውጣት ውድድር አጠናቋል ባጠቃላይም ሁለተኛ በመሆን ጨርሷል።
4. በቱር ዲ ሩዋንዳ በተደረገ ውድድር በስምንት መድረኮች መወዳደር የቻለ እና በ UCI ሴንተር ሁለት ግዜ በመሳተፍ ጨርሷል።