የ2017ዓም የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ዛሬ ተጀመረ።
Dire TOTO ሰኔ ፣ 18 ቀን ፣ 2017ዓም l መቀሌ
በትግራይ ክልል አስተናጋጅነት በኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት አገር አቀፍ የብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር በመቀሌ ከተማ በአዋቂዎች ምድብ የግል ክሮኖ ሜትር ( የሰዓት ጨዋታ ) በወንድና በሴት ውድድር ተጀምሯል።
በሻምፒዮናው ከድሬዳዋ ሁለት ክለቦች ድሬ ቶቶ ብስክሌት ክለብ ፤ ድሬዳዋ ከተማ ክለብ ፤ ከትግራይ ክልል 5 ክለቦች ፤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ሸገር ሲቲ ፤ስልጤ ወራቤ ፤ ኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ እና 5 ክልሎች በአጠቃላይ 16 ክለቦችና ክልሎች በውድድሩ ተሳትፈዋል ።
ውድድሩ እስከ ሰኔ 22/2017 የሚቆይ ሲሆን በነገው ዕለት 2ኛ ቀን ውሎ በወጣቶች ምድብ በወንድና በሴት የግል ክሮኖ ሜትር ጨዋታ ይቀጥላል።