6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታ የብስክሌት  ውድድር በቶቶ ብስክሌት ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

Published on June 1, 2025
56 views

6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታ የብስክሌት  ውድድር በቶቶ ብስክሌት ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ  በድሬዳዋ ከነማ፣ በድሬ ፖሊስና ቶቶ ብስክሌት ክለቦች መካከል ላለፉት  ሳምንታት በድሬዳዋ ከተማ የጎዳና ላይ ክፍት የዙር ብስክሌት ግልቢያ ውድድር  በታላቅ ድምቀት በተካሔደ የመዝጊያ  ጫወታ በግልና በቡድን አጠቃላይ ውጤት በቶቶ ብስክሌት ክለብ ሻምፒዮንነት ፍጻሜውን አግኝቷል ፡፡

በ6ኛው መላው የድሬደዋ ስፖርት የብስክሌት ውድድር የድሬ ዳዋ ከነማ ብስክሌት ክለብ የፍጻሜውን ጫወታ አንደኛ ፣ ድሬዳዋ ፖሊስ ሁለተኛ ሆነው የገቡበትን  ጠንካራ ፉክክር ያደርጉና የስፖርቱን አፍቃሪያንኑና ደጋፊዎቻቸውን ያስደሰቱ ሲሆን በአጠቃላይ የጫወታው ውድድሮች ባስመዘገበው ውጤት ቶቶ ብስክሌት ክለብ አንደኛ በመውጣት ዋንጫውን አንስቷል፡፡

የቶቶ ብስክሌት ክለብ የፊታችን  ሰኔ ወር   2017 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ላይ ለሚደረገው መላው የኢትዮጵያ ክለቦች ስፖርት ውድድር የድሬዳዋ አስተዳደርን ወክሎ የሚሳተሳተፍበትን የአሸናፊነት ውጤት ማስመመዝገቡን ተከትሎ  የክለቡ ምክትል  ፕሬዘዳንት አቶ ዳንኤል ምትኩ የቶቶ ብስክሌት ክለብ ከተመሰረተ ገና አንድ ዓመት ያልሞላው ቢሆንም ከድሬዳዋ አልፈው በሀገር አቀፍና በዓለማቀፍ ደረጃ ሀገራቸውን ወክለው የሚወዳዳሩ የብስክሌት ስፖርተኞችን ለማፍራት ይዘን የተነሳነውን ራእይ ጠንክረን ከሰራን የምናሳካበት ጊዜ ሩቅ አለመሆኑን ያሳየንና ትልቅ የሞራል ስንቅም ሆኖናል ብለዋል ፡፡

በግል ማውንቴን ብስክሌት በቢ ምድብ ይወዳደሩ የነበሩ ብቸኛዋን ሴት ጨምሮ 35 ታዳጊዎችን በቶቶ ብስክሌት ክለብ ስር እንዲካተቱና ወደ ቶቶ ክለቡ  ብስክሌት ማሰልጠኛ አካዳሚ ገብተው እንዲሰለጥኑ  በማድረግም የድሬዳዋ ብስክሌት ስፖርት ዳግመኛ እንዲነቃቃና ተተኪዎችን የማፍራት ውጥናቸውን በተግባር መጀመራቸውን በውድድሩ  የመዝግያ መርሃ ግብር ላይ የቶቶ ብስክሌት ክለብ ቦርድ አመራሮች ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ በተዘጋጀው የርክክብ ስነስርዓት ላይ የድሬ ቶቶ ስፖርት ክለብ  30 ወንድ ታዳጊ ወጣቶች እና አንድ ሴት እንዲሁም ሁለት አሰልጣኞችን የክለቡ ቶቶ አካዳሚ እና በእህት ኩባንያዎቹ ፤ ሀሪፍ ስፖርት ፤ ፈናን ፔይ ፤ 2× ስፖርት እና ድሬ ቲዩብ ድርጅቶች ስም ተተኪዎችን ለማሰልጠን በተካሄደው ርክክብ የክለቡ ቦርድ  ም/ኘሬዚዳንት አቶ ዳንኤል ምትኩ 35 ታዳጊዎችን ተረክበዋል ፡፡ 

በውድድሩ አጠቃላይ ድምር ውጤት በግል የክሮኖሜትር 1ኛ አሚር ጃፈር ፤ 2ኛ ካሌብ በላይ  ከድሬ ቶቶ አሸንፈዋል ፤ 3ኛ ናትናኤል ጥላሁን ከድሬዳዋ ፖሊስ ክለብ በመውጣት የዓመቱን የወርቅ ፤ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ ተቀብለዋል፡፡

በዙር በተካሄደው የሰዓት ድምር ውጤት 1ኛ አሀድ ብርሃን ፤ 2ኛ እየሉም ታደሰ እና 3ኛ ይፍሩ ተሰማ ሦስቱም ተወዳዳሪዎች ከድሬ ቶቶ ክለብ አሸናፊ ሆነው የወርቅ ፤ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያዎችን  አጥልቀዋል፡፡  በዚህ ሻምፒዮና በቡድን ውጤት  ድሬ ቶቶ ክለብ የአጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ድሬዳዋ ፖሊስ ክለብ ሁለተኛ ፤ ድሬዳዋ ከተማ ክለብ 3ኛ  በመሆን ውድድራቸውን  አጠናቀዋል ፡፡

በመለስተኛ  ኮርስ ሚኪያስ ታደስ አሸናፊ በመሆን የወርቅ  ሜዳሊያ እና ዋንጫ ተሸልሟል፡፡ ይሳኩር ፍሬው እና እዩብ ሙሣ በድምር ውጤት 2ኛ እና 3ኛ ሆነው ውድድሩን በማጠናቀቅ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

RELATED

EVENTS

6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታዎች

ፓሊስ መምሪያና ማሪያም ሰፈር | | Dire Dawa | ETHIOPIA

እሁድ ሚያዚያ 26/2017 6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታዎች የብስክሌት ውድድር በመጪው ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል...

04

May

'25

Sunday

Read More

View All Events