በመላው ድሬዳዋ ጨዋታ የብስክሌት ክለቦች ሻምፒዮና ድሬ ቶቶ ክለብ  መሪነቱን አጠናክሯል፡፡

Published on May 18, 2025
100 views

በመላው ድሬዳዋ ጨዋታ የብስክሌት ክለቦች ሻምፒዮና ድሬ ቶቶ ክለብ  መሪነቱን አጠናክሯል፡፡    
Dire Toto ግንቦት 10/2017 ዓ.ም


በ4ኛው ቀን የ6ኛው መላው ድሬዳዋ ጨዋታዎች የብስክሌት ውድድር መርሀግብር  የድሬዳዋ ከተማ ብስክሌተኞቹ እያሱ እሸቱና ይትባረክ ታጀበ ተከታትለው 1ኛና 2ኛ ደረጃን ይዘው ሲያጠናቅቁ የድሬ-ቶቶው ይፍሩ ተሰማ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት የተጀመረው ይሄው የብስክሌት ክለቦችና የግል ውድድር ዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም  የ4ኛ ቀን መርሀግብሩን አካሂዷል፡፡

ልዩ ስሙ ከፖሊስ መምሪያ አንስቶ ማሪያም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲካሄድ የነበረው የብስክሌት ውድድር 40 ዙር ሆኖ በጠቅላላው 100 ኪ.ሜ የሸፈነ ነበር፡፡

በውድድሩ የድሬዳዋ ከተማ ብስክሌተኞቹ እያሱ እሸቱና ይትባረክ ታጀበ 1ኛና 2ኛ በመሆን ተከታትለው ውድድሩን ማጠናቀቅ ሲችሉ የድሬ-ቶቶው ይፍሩ ተሰማ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

በዚህ ሻምፒዮና የአጠቃላይ ድምር እስካሁን በተካሄዱ ጨዋታዎች በቡድን ነጥብ ድሬ ቶቶ ክለብ መሪነቱን ይዟል፡፡

 

RELATED

EVENTS

6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታዎች

ፓሊስ መምሪያና ማሪያም ሰፈር | | Dire Dawa | ETHIOPIA

እሁድ ሚያዚያ 26/2017 6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታዎች የብስክሌት ውድድር በመጪው ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል...

04

May

'25

Sunday

Read More

View All Events