ፍፃሜ ላይ የበላይነት ይዞ ለማጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የድሬ ቶቶ ክለብ አሰልጣኝና ብስክሌተኞች ተናገሩ

Published on May 15, 2025
75 views

በ6ኛው መላው ድሬዳዋ ጨዋታዎች የብስክሌት ውድድር ፍፃሜ ላይ የበላይነት ይዞ ለማጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የድሬ ቶቶ ክለብ አሰልጣኝና ብስክሌተኞች ተናገሩ፡፡

Dire TOTO l  ግንቦት 6/2017

ባለፈው ሚያዚያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም የተጀመረው 6ኛው መላው ድሬዳዋ ጨዋታዎች የብስክሌት ውድድር በ3ቱ ክለቦች መካከል እየተካሄደ ነው፡፡

እስካሁን በውድድሩ የድሬ-ቶቶ  ክለብ በከፍተኛ የነጥብ ልዩነት ድሬዳዋ ፖሊስ እና ድሬዳዋ ከነማ ክለብን እየመራ ይገኛል፡፡

በቀጣይ በሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ የበላይነታቸውን አስጠብቀው ለማጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የድሬ ቶቶ አሰልጣኝ ምስግና ገብርዬ ነግረውናል፡፡

"በእስካሁኑ ውድድር ያሉብንን ክፍተቶች በመለየት በክፍተቶቻችን ላይ ትኩረት አድረገን እንዴት በቀላሉ ተጋጣሚዎቻችንን ማሸነፍ እንችላለን ብለን ልምምድ ሠርተናል … ይሄ ደግሞ ውጤታማ ያደርገናል ብዬ አምናለሁ"

የድሬ-ቶቶ ብስክሌተኛ የሆኑት አሚር ጃፈር  እና የ3ኛው ቀን የጨዋታው  አሸናፊ ኤፍሬም ወሉ  በበኩላቸው "በቀጣይ ጨዋታዎች  ክለባቸው በግልም ሆነ በቡድን አሸናፊ መሆን እንዲችል የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርጉ እንደቆዩ ለቶቶ ሚዲያ ኔትወርክ ተናግረዋል፡፡

በሳምንት አምስት ቀን የብስክሌት ቡድኑ  ልምምድ  በመስራት ላይ እንደሚገኝም ካገኘነው መረጃ ማወቅ ችለናል፡፡

RELATED

EVENTS

6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታዎች

ፓሊስ መምሪያና ማሪያም ሰፈር | | Dire Dawa | ETHIOPIA

እሁድ ሚያዚያ 26/2017 6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታዎች የብስክሌት ውድድር በመጪው ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል...

04

May

'25

Sunday

Read More

View All Events