TOTO l ግንቦት 3 ፣ 2017 ዓ.ም
6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታዎች ባለፈው ሚያዚያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም የተጀመረው የብስክሌት ክለቦች ውድድር ዛሬ ግንቦት 03 ቀን 2017 ዓ.ም የ3ኛው ቀን መርሀግብር ቀጥሎ ተካሂዷል፡፡
በ35 ዙር 87 ኪ.ሜ በሸፈነው ርቀት በድሬደዋ ከተማ ልዩ ስሙ ከፖሊስ መምሪያ እስከ ማሪያም ሠፈር የተካሄደ ነበር፡፡ ሦስቱ የድሬዳዋ የብስክሌት ስፖርት ክለቦች (ድሬ-ቶቶ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ድሬዳዋ ፖሊስ) ተሳታፊ የሆኑበት ውድድር የቶቶ ክለብ ብስክሌተኛው ኤፍሬም ወሉ ሰፊ በሆነ ርቀት ተወዳዳሪዎችን በመምራት አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡
በውድድሩ ላይ ወጣቱ ኤፍሬም ወሉ ከ18 ዙር ጀምሮ ለብቻው ከፊት ሆኖ በረጅምር ርቀት በመምራት ከኋላ ሲከተሉት የነበሩትን ተወዳዳሪዎችን ፍፁም በሆነ የበላይነት አጠናቋል፡፡
6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታዎች ብስክሌት ክለቦች ውድድር የፊታችን ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄድው ጨዋታ ማሳረጊያውን እንደሚያደርግ ከወጣው መርሀግብር ላይ መረዳት ተችሏል፡፡