በ6ኛው መላው ድሬዳዋ ጨዋታዎች የብስክሌት ውድድር የሁለተኛ ቀን መርሀግብር የድሬዳዋ ፖሊስ ብስክሌተኛው ናትናኤል ጥላሁን 1ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀቀ፡: ዛሬ ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የተካሄደው ውድድር የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ነው፡፡
ውድድሩ ከድሬዳዋ እስከ ኦሮሚያ ክልል ጨለንቆ ከተማ እና ቀርሳ ከተማ ላይ የተጠናቀቀ ሲሆን በአጠቃላይ 120 ኪ.ሜ የሸፈነ ነበር፡፡
በውድድሩ የድሬዳዋ ፖሊስ ብስክሌተኛው ናትናኤል ጥላሁን 1ኛ በመሆን አጠናቋል፡፡ የክለብ አጋሩ ብሩክ ፍርድአወቅ 2ኛ እንዲሁም የድሬ ቶቶ ብስክሌተኛው ካሌብ በላይ 3ኛ በመውጣት ውድድሩን ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
ባለፈው እሁድ ሚያዚያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም የተጀመረው 6ኛው መላው የድሬዳዋ ጨዋታዎች የብስክሌት ውድድር እስከ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን የፊታችን እሁድ ግንቦት 03ቀን 2017 ዓ.ም በድሬደዋ ከተማ ልዩ ስሙ መምሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የጎዳና ላይ የዙር ውድድር የሚካሄድ መሆኑን ከወጣው መርሀግብር ለማወቅ ችለናል፡፡