የድሬዳዋ የብስክሌት ክለቦች ውድድር ድሬ ቶቶ ክለብ ተወዳዳሪዎች አሸነፉ

Published on April 26, 2025
9 views

የድሬዳዋ ቶቶ ክለብ ተወዳዳሪዎች አሚር ጃፈር  አሸነፈ ፤ ካሌብ በላይ ከቶቶ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል፡፡ ድሬዳዋ ከነማ በክለብ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል ! 

ባለፉት ወራት ከህዳር 29 ቀን እስከ ሚያዝያ 5 ቀን ፤2017ዓም  ለ3 ሳምንት ሲካሄድ የቆየው የብስክሌት ክለቦች ውድድር  ተጠናቋል፡፡ 

በዚህ ሻምፒዮና የድሬዳዋ ቶቶ ስፖርት ክለብ በውድድሩ  ላይ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክለቡ ጽ/ቤት ዳሬክተር አቶ ዮናስ ተፈራ ከብስክሌት ፌዴሬሽኑ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
   
በድሬዳዋ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ፤ ድሬዳዋ ከነማ ፤ ድሬዳዋ ፖሊስ እና ድሬ ቶቶ ክለቦች መካከል በተካሄደው ሻምፒዮና በከፍተኛ ኮርስ  በአጠቃላይ ድምር በ108 ነጥብ ድሬዳዋ ከነማ የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ዋንጫ ተሸልሟል፡፡ ድሬዳዋ ፖሊስ  እና ድሬ ቶቶ ክለብ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው  አጠናቀዋል ፡፡ 

አሚር ጃፈር ከድሬዳዋ ቶቶ ክለብ  በግል በአጠቃላይ ድምር ነጥብ  አሸናፊ ሆኗል፡፡ እያሱ እሸቱ ከድሬዳዋ ከነማ 2ኛ ሆኗል፡፡ 
ካሌብ በላይ ከድሬዳዋ ቶቶ ክለብ 3ኛ በመሆን የወርቅ ፤ የብር እና የነሐስ  ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ 

በታዳጊ ወጣቶች መካከል በB ምድብ ሚኪያስ ፋንቱ  አንደኛ በመውጣት ዋንጫ ተሸልሟል፡፡ 2ኛ ረመዳን በያን ፤ 3ኛ ሚኪያስ ታደስ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡ 

በሽልማት ስነስርዓት የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ማሳተፍና ማልማት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር  አቶ ኢብሳ ዱሪ እና የውድድር ተሳትፎ  ኬዝ ቲም ቡድን መሪ ወ/ሮ ሙና ሁሴን ለውድድሩ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የምስክር ወረቀት፤ ለአሸናፊዎች የወርቅ ፤ የብር ፤ የነሐስ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ሽልማት አበርክተዋል፡፡ 

የ2017ዓም የአስተዳደሩ የብስክሌት ክለቦችና የግል ሻምፒዮና ውድድር በቅርቡ በድሬዳዋ እንደሚጀመር ታውቋል፡፡